ASC Logo

Amhara Region

Supreme court

ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከፍተኛ አመራሮቹ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምቹ የሥራ ከባቢን ለመፍጠር እና የዳኝነት አገልግሎትን ለማሻሻል እየሰራቸው ስላሉ የለውጥ ስራዎች በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ከፍተኛ አመራሮቹ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸው የለውጥ ስራዎች ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣ ተገማችና ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት መብትን እውን የሚያደርጉ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በተያያዘም የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ አባላት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የዳኝነት አገልግሎትን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን ፣ ከባለጉዳዮች እና ዳኞች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በባለጉዳዮች በኩል በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተጀመሩ ስራዎች የዳኝነት አገልግሎትን ውጤታማነት የሚያረጋግጡ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉ ሲሆን ፣ ሊስተካከሉ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በመጥቀስ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ ዳኞች የዘመናት ጥያቄ የነበረው የዳኞች ከለላና ጥበቃ በሕግ እውቅና መሰጠቱ ፣ ምቹ የሥራ ከባቢ በመፈጠሩ ክርክሮችን በግልጽ ችሎት ማካሄድ መቻሉ እና የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍናን፣ ተገማችነትን ለማስፈን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ዳኞች ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ አልፎ አልፎ የፍርድ ቤትን ውሳኔዎች ለመፈጸም እና ለማስፈጸም የእምቢተኝነት አዝማሚያ መታየቱ፣ በዳኝነት ነጻነት ላይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት መታየት በችግርነት በመጥቀስ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸው ጅምር የለውጥ ስራዎች የዳኝነት አገልግሎትን ቅልጥፍና፣ ተገማችና ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን በመግለጽ አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ እየተሰሩ ያሉ ጅምር ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *