ASC Logo

Amhara Region

Supreme court

About


መልዕክት ከፕሬዝዳንቱ

Boss

Statement from the President of the Amhara Supreme Court
በዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ ፍ/ቤቶች ሶስተኛ የመንግስት አካል ናቸው፡፡ ዋና ተልዕኳቸውም ነጻና ገለልተኛ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው። ይህንን ትልቅ ሃላፊነት ለመወጣትና ተልዕኳቸውን ለማሳካት በሰዎች መካከል በዘር፣ በፆታ፣ በማህበራዊ አቋም እና በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ልዩነት ሳይኖር በገለልተኝነት እና በፍትሃዊነት ነፃ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል።  
በኢትዮጵያ እስከ 1900 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ባሕላዊ የሽምግልና የዳኝነት ስርዓት እና  ፍትሃ ነገስትን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሕጎችን መሰረት ያደረገ ዳኝነት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከ1900 ዓ.ም በኋላ  በተለይም ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ ዘመናዊ የሕግ ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን በ1987 ዓ.ም አዲስ የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት ተከትሎም  አገራችን በምትከተለው የፌደራል ቅርፀ መንግስት አወቃቀር  መሰረት የዳኝነት አገልግሎት ትይዩ ሆነው  በፌደራል እና በክልል በተቋቋሙ ፍ/ቤቶች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የክልል ፍ/ቤቶች በክልል ሕገ-መንግስት በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት በክልል ጉዳዮች ላይ  እና በፌደራል ሕገ-መንግስት በተሰጣቸው ውክልና ደግሞ በፌደራል ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ስልጣን አላቸው።
የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች በፌደራል ሕገ-መንግስት፣ በ1987 በወጣዉ እና በ1994 ዓ.ም በተሸሻለዉ የክልል ህገ-መንግስት እና በተለያየ ጊዜ በወጡ ዝረዝር የሕግ ማዕቀፎች የተሰጣቸውን ነፃ የዳኝነት አገልግሎት የማረጋገጥ ተልዕኮ ለመወጣት ሲሰሩ ቆይተዋል። በዚህም ከ30 አመት በላይ ባስቆጠረ የዳኝነት አገልግሎት ሂደት የክልሉ ፍ/ቤቶች በዳኝነት ጥራት እና  የላቁ ዳኞችን  በማፍራት ይታወቃሉ።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን የክልሉን ፍ/ቤቶች ጥንካሬ ለማስቀጠልና አቅማቸውን ይበልጥ ለማሳደግ፤ እንዲሁም በሂደት የታዩ ክፍተቶችን በአግባቡ በመሙላት ለሕብረተሰቡ የተሻለ የዳኝነት አገልልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ፍ/ቤቶች ሰፊ የለውጥ ሥራዎች እና ፕሮጀክቶች እንዲተገብሩ አድርጓል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም  በሃገር ደረጃ ተምሳሌት ለመሆን እና በመካከለኛ እና ረጅም ጊዜ ደግሞ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ተጠቃሽ ፍ/ቤቶችን ለመገንባት ራዕይ አንግቦ  የተለያዩ ስትራቴጅዎችን በመቅረፅ እየሰራ ይገኛል ።
በዚህም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ (በ2017 ዓ.ም) ብቻ  አግልገሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጅ በማስደግፍ፣ ምቹ የማስቻያ እና የሥራ ቦታዎችን በመፍጠር፣ የዳኞች ያለመከሰስ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ማድረግን ጨምሮ፣ የፍ/ቤቶችን ነፃነት የሚጋፉ የኮሚቴ አደረጃጀቶችን በማስቀረት፣ በፍ/ቤቶች በራሳቸው እና በምክር ቤቶች ብቻ የሚመሩ በማደረግ የዳኝነት ነፃነትን ለማስከበር የሚረዱ ወሳኝ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ፍ/ቤቱ የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች ዘላቂነት የሚያረጋግጡ እና ተቋማዊ የሚያደርጉ የሕግ ማዕቀፎች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ የባህል ፍ/ቤቶችን ማቋቋምን ጨምሮ አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓቶችን የሚያጠናክሩ እርምጃዎችም ተወስደዋል፡፡ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ከዳኝነት አካሉ አልፎ አጠቃላይ የክልሉን የፍትህ ሥርዓት ውጤታማ  ለማድረግ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የትብብር መድረክን (Joined Up Justice Forum) የሰብሳቢነት ኃላፊነቱን በአግባቡ በመወጣት አስደማሚ የሚባሉ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል፡፡  ይህም በዳኞች፣ በፍ/ቤት ሠራተኞች እና በአጠቃላይ በፍ/ቤቱ ማህበረሰብ  እና በፍትህ አካላት ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት ፈጥሯል።
በተለይም በፍ/ቤቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2018 ዓ.ም  ለ10 ተከታታይ ቀናት (ከመስከረም 20 እስከ 29 ) በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ “የጋራ ራዕይ ለጠንካራ የዳኝነት ሥርዓት” በሚል መሪ ቃል በባህር ዳር ከተማ የተካሄደዉ እና ከ 2400 በላይ የክልሉ ዳኞች የተሳተፉበት  የዳኞች ኮንፈረንስ፤ ፍ/ቤቱ የጀመራቸዉን የለዉጥ  ሥራዎች እስከ ወረዳ ማድረስ የተቻለበት እና በጋራ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የተደረሰበት ሲሆን በዳኞች እና በፍ/ቤቱ ሠራተኞች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የሥራ ተነሳሽነትን የጨመረ ሆኗል፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለሰዉ ሃይል ልማት ከፍተኛ ቦታ በመስጠት በልዩ ትኩረት እየሰራ ሲሆን የክልሉ ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት ለጠቅላይ ፍ/ቤት ተጠሪ ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 299/2017 እንደገና ከተቋቋመ በኋላ ይህ ተቋም በሕግና ፍትህ ጉዳዮች የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ለማስቻል የተለያዩ ስትራቴጅክ ውሳኔዎችን በመወሰን ድጋፎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡ 
የክልሉ መንግስት  በ2017 እና 2018  በጀት ዓመት በአንፃራዊነት የተሻለ በጀት በመመደብ እና የፍ/ቤቱን የለውጥ ሥራዎች በሕግ ማዕቀፍ በማስደገፍ ረገድ በጎ ጅማሮዎች የታዩበት ነው። ወደፊትም በዚሁ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡ ሌሎች የሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ከፍ/ቤት ጋር ተቀራርበው መስራት የጀመሩበትና የተሻለ ድጋፍ ያሳዩበትም ነው። ለዚህም ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ከፍተኛ ምስጋና አለው።
በቀጣይ ጊዜአት በጠቅላይ ፍ/ቤት እና በፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩት ሥር ነቀል በሆነ መልኩ የአሰራር እና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ በማድረግ የተጀመሩ የለዉጥ ሥራዎችን በፅኑ መሰረት ላይ የማስቀመጥና ለተቋም ግንባታ መሰረት የመጣል ሥራዎች የሚከናወኑ  ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የባሕል ፍ/ቤቶችን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሥራ ማስጀመር እና ዘላቂነታቸዉን ማረጋገጥ፣ የክልሉን ሕዝብ የሚመጥን እና ደረጃዉን የጠበቀ አዲስ የጠቅላይ ፍ/ቤት ሕንጻ መገንባት፣ ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ማሰልጠኛ ተቋም መገንባት፣ የሕግ የበላይትና የሰላም ማዕከል መገንባት፣ የተከላካይ ጠበቆች አገልግሎት ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ማድረግ፣ የዲጅታላይይዜሽን ሥራችንን የበለጠ  አጠናክሮ ማስቀጠል ተጠቃሽ ትኩረት የሚደረግባቸው ተግባራት ይሆናሉ፡፡
ፍ/ቤታችን ያስቀመጠዉን ራዕይ ለማሳካት እና ተልዕኮዉን ለመፈጸም ከምግዜዉም በላይ በከፍተኛ ትጋትና ቁረጠኝነት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በሌላ በኩል ነፃ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ፣  ተገማች እና ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎትን የማረጋገጥ ጉዳይ በፍርድ ቤቱ ጥረት ብቻ  የሚሳካ አይደለም። ስለሆነም ሁሉም የፍትህ አካላት፣ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የሕጉ ማህበረሰብ፣ ማስረጃ ሰጭ ተቋማትን እና አጠቃላይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ፍ/ቤቱ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ እንዲደግፉ በራሴና በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ስም ጥሪየን አቀርባለሁ ።
 
ፍትህን በታማኝነት !
ተምሳሌት የሆኑ ፍ/ቤቶችን ለመገንባት እንተጋለን !
 
ዓለምአንተ አግደው ወንድሜነህ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት
 

more about us

OUR HISTORY

The establishment of the Amhara Regional Supreme Court is related with the establishment of Region 3 (Three) in the aftermath of the fall of the Derg Regime and the coming into power of the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) in 1991. It is to be recalled that immediately after the fall of the Derg government, a Transitional Government of Ethiopia was established in July 1991 in light of the Transitional Period Charter of Ethiopia. Region 3 (Three), the present Amhara Regional State, was one of the 14 National/Regional Self-Governments established as per Arts 3 and 9 (1) of the National/Regional Self-Governments Establishment Proclamation No. 7/1992. The Constitution of the Transitional Government of Region Three, Proclamation No.2/1993, constituted Regional legislative, executive and judicial organs under Art 21. This Transitional Constitution explicitly provided that judicial power in the Region as being vested in the Regional Supreme Court and other lower zonal and wereda (district) courts of the Region. 

In accordance with the Constitution of the Transitional Government of the Region, the then legislative body (the Council of the Transitional Government of Region Three) thus issued for the first time in the history of the Amhara Regional State a proclamation that provided for the establishment of courts in the Region. This proclamation referred to as the “Proclamation to Establish the Courts of the Transitional Government of Region Three, Proclamation No. 3/1993” and which entered into force as of the 25th of June 1993 explicitly established the three-tiered levels of courts as the Regional Supreme Court, Zonal High Courts and Wereda Courts. Immediately thereafter, the President of the Regional Supreme Court was appointed by the Transitional Regional Council and that was followed by the appointment of other judges to the three levels of courts. What was put in place during the Transitional period continued with the re-establishment of the Amhara National Regional State Supreme and its lower zonal and wereda courts in view of the establishment of the Amhara National Regional State as per the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (1994) and the Constitution of the Amhara National Regional State (1995).



Contact

Our mission

Ensuring justice, upholding the rule of law, and providing fair, transparent, and efficient judicial services to safeguard the rights and freedoms of all.

Our Vision

Ensuring justice, upholding the rule of law, and providing fair, transparent, and efficient judicial services to safeguard the rights and freedoms of all.

Our Value

Ensuring justice, upholding the rule of law, and providing fair, transparent, and efficient judicial services to safeguard the rights and freedoms of all.

Previous Presidents

photo_5875400083246270431_y
Mr. Adafrie Gebeyehu
President
8


9


7


10


photo_5875400083246270432_y
Ambassador Ali Suleman
President
11
Mr. Abiye Kasahun
President
1
Yearly Cases
1+
Supreme Court judges
1
Supporting Staffs
1
Administration Staff