በልዩ ልዩ የአይ.ሲ.ቲ የሥራ መደቦች ላይ ለመቀጠር ለአመለከታችሁ በሙሉ
ባሕርዳር ፣ ነሐሴ 08/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በየደረጃው በሚገኙ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የጀመራቸውን የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች የሚያግዙ በዘርፉ የዳበረ ብቃት፣ የሙያ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ባለሙያዎች ለመቅጠር በ 27/04/2018 ዓ.ም ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል።
የተመዝጋቢዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምልመላ፣ የፈተና እና አጠቃላይ የቅጥር ሂደቱን በዘርፉ ብቃቱ፣ ልምዱ እና አስፈላጊው የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ብቁ ባለሙያዎች በጥንቃቄ ለመለየት ያደረገው ጥረት ለቀጣዩ የውድድር ሂደት የሚመረጡ ተወዳዳሪዎችን ለመለየት እስካሁን የቆየ ሲሆን፤ በዛሬው እለት ለቀጣዩ የውድድር ሂደት የተመረጡ አመልካቾችን ይፋ አድርጓል።
ስለሆነም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተለያዩ የአይ.ሲ.ቲ የስራ መደቦች ላወጣቸው የቅጥር ማስታወቂያዎች ያመለከታችሁ አመልካቾች፣ ከዚህ በታች በተዘረዘረው አግባብ ለቀጣዩ የፈተና ሂደት መመረጣችሁን አንድታረጋግጡ እያሳሰብን፣ የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልታችሁ ስማችሁ ያልተካተተ ተወዳዳሪዎች ከስር በተቀመጡት አድራሻዎች ቅሬታችሁን እንድታቀርቡ እናሳውቃለን።
Telegram: https://t.me/Spc2016
Email: public.relation@amhsc.gov.et