




ምክትል ርእሰ መሥተዳደሩ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የሕንጻ እድሳት እና የሚሠሩ አዳዲስ ማስፋፊያዎችን ተመልክተዋል። በምልከታው ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለም አንተ አግደው እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ምክትል ርእሰ መስተዳደር አብዱ ሁሴን ሁሴን (ዶ.ር) ውበቱን እና የተገልጋዮችን ምቾት በጠበቀ መልኩ እየተሠራ ያለውን የእድሳት ሥራ አድንቀዋል።
የሕንጻው እድሳት ዘመናዊ አሠራሮችን እና የዲጅታል አገልግሎትን በማካተት እየተሠራ መኾኑ አገልግሎት አሰጣጡን እንደሚያዘምንም ተናግረዋል።
የእድሳት እና የማስፋፊያ ሥራው በፍጥነት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በክልሉ መንግሥት በኩል አሥፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለም አንተ አግደው የእድሳት ሥራው ኋላቀር የነበረውን አሠራር በሚያዘምን መልኩ እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል።
በውስጡም ሰው ተኮር የኾኑ መሰረተ ልማቶችን አካትቶ የተሠራ ነው ብለዋል።
