ባህርዳር፣ ሐምሌ 30/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው፣ ተደራሽ፣ ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ፣ ፍርድ ቤቶች የህዝብ አመኔታን ያተረፉ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የለውጥ ስራዎችን በስፋት እየሰራ ሲሆን
በተለያየ ጊዜ ከፌደራል እና ከክልል የሚመጡ እንግዶች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የለውጥ ስራዎች መመልከት ችለዋል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የለውጥ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በጉብኝታቸውም፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዲጂታላይዜሽን ስራዎች እና ስማርት ችሎቶችን፣ የዲጂታል አንድ ማእከል አገልግሎት፣ ዘመናዊ የሕጻናት ማቆያ፣ ግልጽ ችሎት የሚከናወንባቸውን የችሎት አዳራሾች፣ የጥሪ ማዕከል እና ሌሎች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን ተመልክተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያዩት የሪፎርም ስራ ተስፋ እንደሰጣቸው ገልጸው፣ ይሄንን ባጭር ጊዜ እውን ላደረጉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።







