ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቫይሮንመንታል ፕሮቴክሽን ኦርጋናይዜሽን (አስዴፖ) በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቫይሮንመንታል ፕሮቴክሽን ኦርጋናይዜሽን (አስዴፖ) በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜ 2/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አስዴፖ በትብብር በመስራት የዳኝነት እንዲሁም የፍትህ ሥርዓቱን ውጤታማነት ማደበር የሚያስችል ስምምነት፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው እና የአስዴፖ ዋና ዳይሬክተር አቶ ምህረትአብ በላይ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነት ሰነዱ ተቋማቱ በፍርድ ቤቱ የሚደረጉ የሠው ሃብት አቅም ግንባታ ስራዎች፣ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ አካላት ጥበቃ በተለይ የህፃናት መብት ጥበቃ፣ የፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍል ጥበቃ፣ ዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተሰሩ ስራዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ያብራሩ ሲሆን፣ የአስዴፖ ዋና ዳይሬክተር ፍርድ ቤቱ በአጭር ግዜ ያከናወናቸውን ተግባራትን በማድነቅ ተቋማቸው በተሰማራባቸው ዘርፍ ላይ ፍርድ ቤቱን ለማገዝ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *