ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 23/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክተር፣ የዳኝነት አገልግሎት አስተባባሪ፣ የችሎት አገልግሎት ቲም ሊደር እንዲሁም የሸገር ሲቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት፣ ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በፍርድ ቤቶች ሁሉ አቀፍ የለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የክልሉን ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ በመሠረታዊነት ለማሻሻል እያከናወናቸው ያሉ የአሠራር ማሻሻያዎችን በተመለከተ ለኃላፊዎቹ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ከኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጡ እንግዶች በበኩላቸው፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤታቸው አሠራሩን ለማዘመን እየተገበራቸው ያሉ ሥራዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ዝርጋታ፣ ለዳኞች፣ ሰራተኞች እና ባለጉዳዮች ምቹ የሥራ ከባቢዎችን ለመፍጠር ያከናወናቸው የተቋም ግንባታ ሥራዎች፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እና በሌሎች የአገልግሎት መስጫ ማሻሻያዎች ላይ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመጡ ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ከተደረገላቸው ገለጻ እና ማብራሪያ በተጨማሪ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሁሉአቀፍ የለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች ተዘዋውረው የተመከለቱት ኃላፊዎቹ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የለውጥና የማሻሻያ ስራዎችን ትግበራ በጀመረ በሁለት እና ሶስት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው ስኬት እና ያከናወነው ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በግልጽ ችሎት የሚዳኙበትን ምቹ እና ዘመናዊ የችሎት አዳራሾች፣ የተቋሙን ዲጅታል አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የጥሪ ማዕከል፣ የሕጻናት ማቆያ፣ ሕጻናት የያዙ ባለጉዳዮች የሚያርፉበትን ምቹ ስፍራ ጨምሮ፣ የፍትሕ ሙዚየም እና ሌሎችን ሥራዎችን የጎበኙት ኃላፊዎቹ፣ ለትውልዱ መማሪያ ሆኖ የተገነባው የፍትሕ ሙዚየም ብዙ ነገር የሚማሩበት መሆኑን እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የለውጥና የማሻሻያ ትግበራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናውን ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *