ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የፍትሕ ተደራሽነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ከአየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የፍትሕ ተደራሽነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ከአየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 15/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው፣ በኢትዮጵያ ከአየርላንድ ኢምባሲ አምባሳደር ክቡር ሲራን ማደን ጋር የፍትሕ ተደራሽነት ማጠናከር እና የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ምቹ እና ቀልጣፋ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ክቡር ፕሬዝደንቱ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአማራ ክልል ፍርድ ቤት የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓቱን ዘመናዊ እና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እስካሁን ያከናወናቸውን ስራዎች ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመራቸውን ማሻሻያዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ከኢምባሲው ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎትም ገልጸውላቸዋል።

በክልሉ የፍትሕ ሥርዓቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ፣ የባሕል ፍርድ ቤቶችን የማስፋፋት እና ማጠናከር እንዲሁም አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎችን እና የተከላካይ ጠበቆችን ማጠናከር አስመልክቶ የተወያዩ ሲሆን፣ በዘመናዊ የዳኝነት መስጫ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የፍትሕ ሥርዓቱን ተደራሽ የማድረግ አስፈላጊነት ላይ መክረዋል።

በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ሲራን ማደን በበኩላቸው፣ ክቡር ፕሬዝደንቱ ላደረጉላቸው ገለጻ እና አቀባበል አመስግነው፣ ኢምባሲያቸው የፍትሕ ስርዓቱን ይበልጥ ተደራሽና ዘመናዊ ለማድረግ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በውይይታቸው ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሁሉአቀፍ የለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች የጎበኙት አምባሳደር ሲራን፣ ባዩት የለውጥና የማሻሻያ ሥራ መደሰታቸውን ገልጸው ክቡር ፕሬዘዳንቱ እና በዚህ የለውጥ ሥራ የተሳተፉ አካላትን ሁሉ አመስግነዋል፤ በፍ/ቤቱ የለውጥ ሥራ ፕሮጀክቶች ላይ በቀጣይ ተጨማሪ ውይይት እንደሚደረግም ገልፀዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *