ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

“የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ባለፉት 2 ዓመታት የተሠራው ሥራ ከፍተኛ ነው” አቶ ጎሹ እንዳላማው- የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

“የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ባለፉት 2 ዓመታት የተሠራው ሥራ ከፍተኛ ነው” አቶ ጎሹ እንዳላማው- የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

ባህር ዳር፣ መስከረም 20/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ፍርድ ቤት ዳኞች 2ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዛሬው እለት የተጀመረ ሲሆን፣ የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው፣ በመድረኩ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የአማራ ሕዝብ ለሕግ እና ፍትሕ ትልቅ ቦታ ያለው መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፣ የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሠራው ሥራ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመኑን የዋጀ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሠራው ሥራ የፍርድ ቤቱን ክብር ያስጠበቀ ብቻ ሳይሆን፣ ለሕዝብ ትልቅ መፍትሔ የሰጠ፣ ፍትሕ ጠያቂው ማሕበረሰብ በቅርበትና በላቀ የአገልግሎት ጥራት ፍትሕ እንዲያገኝ ያስቻለ እና እውቅና የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመደበኛ ሥራው በተጨማሪ፣ የከተማው የኮሪደር ልማት ላይ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ ለሌሎች አርአያነት ያለው የማህበራዊ ግዴታውን የተወጣ መሆኑን እና ይህም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሁለንተናዊ መስክ

ተምሳሌት እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የጉባኤውን ተሳታፊዎች እንኳን ደሕና መጣችሁ ያሉት አቶ ጎሹ እንዳላማው፣ የባሕር ዳር ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *