ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በትላንትናው እለት ለክልሉ ምክር ቤት ካቀረቡት ሪፖርት የተወሰደ
ባሕርዳር፣ ሐምሌ 25/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለ 15 ባሕላዊ ያለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች እውቅና በመስጠት ስራ እንዲጀምሩ ካደረገ ወራቶች ተቆጥረዋል።
የባሕል ፍርድ ቤቶቹ ስራ በጀመሩባቸው የተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ፍትሕን ለማሕበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ ፣ ተገልጋዮች ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማስቻል ላይ ናቸው።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጥናት ለለያቸው የክልሉ 15 ባሕላዊ ያለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች እውቅና ሰጦ በይፋ ስራ በጀመሩ በወራት ጊዜ ውስጥ እስካሁን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ተከናውነዋል ![]()
15 የባሕል ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 298/2017 እውቅና አግኝተዋል።
በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሚመራ የባሕል ፍርድቤቶች አማካሪ ምክር ቤትና ጽሕፈት ቤት ተቋቁሟል።
የባሕል ፍርድ ቤቶች የሚመሩበት መመሪያ፣ የስልጠና ሰነድ፣ የኮምዩኒኬሽን ስትራቴጂ እና የአማካሪ ምክር ቤት የውስጥ አሰራሮች ተዘጋጅተው ወደ ሥራ ገብተዋል።
በሁሉም ዞኖችና በ98 ወረዳዎች የአማካሪ ምክር ቤቶች ተቋቁመዋል።
7,318 የባሕል ፍርድ ቤት ዳኞች ተመርጠዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 538 ሴቶች ናቸው።
በ1,377 ቀበሌዎች የባሕል ፍርድ ቤቶች ተቋቁመው ስራ ጀምረዋል።
1,195 መዝገቦች ቀርበው 1,048 እልባት አግኝተዋል።
943 የበጎ ፈቃድ ፀሐፊዎች ተመድበው የውሳኔ መዝገብ ሥርዓት ተጠናክሯል።
3,145 ሽማግሌዎችና 488 ፀሐፊዎች በ649 ቀበሌዎች ስልጠና ወስደዋል።
21,045 የሚሆኑ የማኅበረሰብ አባላት ስለ ባሕል ፍርድ ቤቶች ግንዛቤ አግኝተዋል።
736 የባሕል ፍርድ ቤት የቀበሌ ማዕከላት ተቋቁመዋል።
በደሴ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር እና ደብረ ብርሃን ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መድረኮች ተካሂደዋል።
በግንቦትና ሰኔ 2018 ብቻ 2,416 ሰዎች ባለጉዳይ የሆኑባቸው 1195 መዝገቦች በባሕል ፍርድ ቤቶች ተስተናግደዋል፤ በዚሕም 29,943,877.50 ብር የባለጉዳዮችን ወጪ መቆጠብ ተችሏል።
ከሰር የተያያዙት ፎቶዎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሕብረተሰቡ የባሕል ፍርድ ቤት ዳኞችን በየአካባቢው ሲመርጥ ለማሳያነት የቀረቡ ናቸው።























