ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 ስትራቴጂክ እቅድ እና የሶስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን  ትግበራ አፈጻጸም ውይይት ላይ የተገኙ የጎንደር ከተማ ተሳታፊዎች  ለክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ስጦታ አበረከቱ

በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 ስትራቴጂክ እቅድ እና የሶስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን  ትግበራ አፈጻጸም ውይይት ላይ የተገኙ የጎንደር ከተማ ተሳታፊዎች  ለክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ስጦታ አበረከቱ

ባሕር ዳር፣ ሐምሌ 10/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና በሶስት ዓመቱ የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት ከተወጣጡ ተሳታፊዎች ጋር መወያየቱ ይታወቃል።

በውይይቱ ወቅት ከተገኙ ተሳታፊዎች መካከልም ከጎንደር ከተማ የመጡ ተሳታፊዎች ተጠቃሾች ናቸው።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የክልሉን የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓት በመሰረታዊነት ለመለወጥ የጀመሯቸው የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግበዋል ያሉት ተወካዮቹ፣ ክቡር ፕሬዝደንቱ ለሌሎች ተቋማት እና የክልሉ ከተሞች አመራሮች መነቃቃትን የፈጠረ ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል።

ክቡር ፕሬዝደንቱ ከራሳቸው ተቋም አልፈው ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ምቹ የመኖሪያና የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ከተማ አስተዳደሩና የከተማዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ተወጠዋል ያሉት የጎንደር ከተማ ተሳታፊዎች፣ ለክቡር ፕሬዝደንቱ ስጦታ አበርክተውላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *