ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና የሶስት ዓመት  ትራንስፎርሜሽን ትግበራ አፈጻጸም ውይይት ላይ የተገኙ አጋርና ባለድርሻ አካላት  የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ምቹ የስራ ከባቢ ጎበኙ

በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና የሶስት ዓመት  ትራንስፎርሜሽን ትግበራ አፈጻጸም ውይይት ላይ የተገኙ አጋርና ባለድርሻ አካላት  የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ምቹ የስራ ከባቢ ጎበኙ

ባሕርዳር፣ ሐምሌ 10/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና የ ሶስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ላይ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር መውያየቱ ይታወሳል።

በውይይቱ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶችና የሕግ ምሁራን፣ ጠበቆች፣ የክልሉ የተለያዩ ቢሮዎች ሀላፊዎች፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፣ ከውይይቱ ጎን ለጎንም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር እና ተቋሙን የዘመናዊ ዳኝነት አገልግሎት መስጫ ማእከል ለማድረግ የዘረጋቸውን የዲጅታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለሰራተኞችና ለተገልጋዮ ህብረተሰብ ምቾትን የሚሰጥ የስራ ከባቢ መፍጠር መቻሉን የተናገሩት የውይይቱ ተሳታፊ ጎብኝዎቹ፣ የክልሉን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ የዲጅታል ቴክኖሎጅ የታገዘ ለማድረግ ክቡር ፕሬዝደንቱ ለወሰዱት ቁርጠኛ አቋምና የመሪነት ጥበብ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ተገልጋዮች ሁሉንም የአገልግሎት አይነቶች በአንድ የሚያገኙባቸው የዲጅታል አንድ ማእከል፣ የርቀት ክርክር የሚካሄድባቸው ስማርት ችሎቶች፣ምቹ እና ዘመናዊ የሕጻናት ማቆያ፣ ባለጉዳዮች ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መምጣት ሳይጠበቅባቸው መዝገብ የሚከፍቱባቸው፣ ቀጠሮ የሚከታተሉባቸው እና ስለ ጉዳያቸው ሂደት መረጃ የሚጠይቁበትን ጨምሮ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ስለፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ ማንኛውም ጥቆማ የሚሰጡበትን የተደራጀ የጥሪ ማእከል ተዘዋውረው የጎበኙት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አጋርና ባለድርሻ አካላት፣ባዩት ነገር መደነቃቸውን ገልጸው፣ ሌሎች ተቋማትም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ስራዎች በአርአያነት መከተል እንደሚገባቸው ሀሳባቸውን ሰጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *