ባሕርዳር፣ ሐምሌ 10/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ፍርድ ቤቶች የ2018 ስትራቴጂክ እቅድና የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ላይ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በተወያየበት ወቅት የተለያዩ ሀይማኖት ተቋማት አባቶች በውይይት መድረኩ ተገኝተዋል።
በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ አባታዊ ቡራኬያቸውን የሰጡት የሀይማኖት አባቶቹ፣ የዳኝነት እና የፍትሕ ተቋማት ለማሕበረሰቡ ትክክለኛ ዳኝነት እና ፍትሕን የመስጠት አደራ የተጣለባቸው መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይሄንን አደራ ለመወጣት እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥረት አድንቀዋል።
ከውይይቱ ጎን ለጎን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሁሉአቀፍ የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች በአካል የተመለከቱት የሀይማኖት አባቶቹ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ለአመታት እንደሚያውቁት ተናግረው፣አሁን ላይ የተደረገው የማሻሻያ ስራ ተቋሙን እንደ አዲስ የሰራው ነው ብለዋል።





