ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የአማራ ክልል ፍትሕና ሕግ ኢኒስቲትዩት እጩ ዳኞችና አቃቢ ሕጎች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፍትሕ ሙዚየም፣ ምስለ ችሎት ውድድር አካሄዱ

የአማራ ክልል ፍትሕና ሕግ ኢኒስቲትዩት እጩ ዳኞችና አቃቢ ሕጎች በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፍትሕ ሙዚየም፣ ምስለ ችሎት ውድድር አካሄዱ

ባህርዳር፣ ግንቦት 27/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን የዳኝነት ስርዓት በመሰረታዊነት ለማሻሻል፣ ተግባራዊ እያደረጋቸው ካሉ  የለውጥ ስራዎች አንዱ፣ የሀገሪቱን እና የክልሉን ቀደምት የዳኝነት ስርዓት የሚያሳዩ የሰነድ፣ የምስል እና የድምጽ እንዲሁም፣ የቁስ ሀብቶችን ማሰባሰብ እና  ፣በሙዚየም ማደራጀት ነው።

ወደ ሙያው ለመቀላቀል በሂደት ላይ ያሉ እጩ ዳኞች እና አቃቢ ህጎች፣ በተግባር ተኮር ልምምድ የታገዘ  በቂ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያግዝ፣ የምስለ ችሎት ማስቻያ የሙዚየሙ አካል በማድረግ ፣አቅማቸውን እንዲያዳብሩ በማድረግ ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ በክልሉ እና በሀገሪቱ የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓት ላይ፣ ምርምር የሚያካሂዱ ተመራማሪዎችም በዘርፉ ላይ በቂ የታሪክ ማጣቀሻ እንዲያገኙ የሚረዱ፣ ጥንታዊ አዋጆችን፣ደንቦችን፣ መመሪያዎችን፣ፎቶዎችን፣ ህገ-መንግስት እና ሌሎች፣ ከዳኝነት እና ከፍትሕ ስርዓቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፣የሚዳሰሱ ታሪካዊ ሀብቶች በማሰባሰብ እና፣ በማደራጀት ላይ ይገኛል።

ከሌሎች የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች ትይዩ፣ በሀገር አቀፍ  እና በክልሉ ደረጃ  በዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓቱ ላይ የነበሩ፣ አጠቃላይ ሂደቶችን ትውልድ ተሻጋሪ ለማድረግ  እየሰራ የሚገኘው  ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የሙዚየሙ አካል የሆነውን የምስለ ችሎት ማስኬጃ አዳራሽ፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የአማራ ክልል የሕግና ፍትሕ ኢኒስቲትዩት እጩ ዳኞችና አቃቢ ሕጎች፣ የምስለ ችሎት ውድድር እንዲያካሂዱበት፣ አድርጓል።

 በውድድሩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት፣ የአማራ ክልል ሕግና ፍትሕ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶር ደሴ ጥላሁን፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የክልሉን የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓት በዘላቂነት ለማሻሻል፣ እየተገበራቸው ያሉ ለውጦችን አድንቀው፣ በክልሉ የዳኝነት እና የፍትሕ ስርዓት ውስጥ፣ ብቃት ያላቸውን ዳኞችና አቃቢ ህጎች ፣እንዲሁም ሌሎች የፍትሕ ባለሙያዎች ለማፍራት፣ ኢኒስቲትዩታችን በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች በተግባር ለማየት፣ የሙዚየሙ አካል ሆኖ የተገነባው የምስለ ችሎት አዳራሽ፣ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

በሙዚየሙ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ውድድር በማዘጋጀታችን ደስታ ይሰማናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለክልሉ የዳኝነት እና የፍትሕ መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ ያለውን፣ የምስለ ችሎት አዳራሽ መገንባቱ  ፣የኢኒስቲትዩታቸው ሰልጣኞች  በሙያው የዳበረ ልምድ ካላቸው ዳኞችና አቃቢ ህጎች ፣ልምድና ተሞክሮ እንዲጋሩ ፣የሚያስችል ነው ብለዋል።

በውድድሩ ላይ የተገኙ ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የፍትሕ ቢሮ  አቃቢ ሕጎች ፣በትምህርት እና በስራ ላይ ያገኙትን ልምድ እና እውቀት ፣ ለተወዳዳሪዎችና ለሌሎች ተሳታፊ እጩ ዳኞችና አቃቢ ሕጎች፣ አጋርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *