ባህርዳር ፣ ግንቦት 17/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተገልጋዮችን ወጭ፣ጊዜና እንግልት የሚቀንሱ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየዘረጋቸው ካሉ ዘመናዊ አሰራሮች መካከል ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት በአካል መምጣት ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ስፍራ ሆነው ስለመዝገቦቻቸው ሁኔታ እና ሌሎች የፍርድ ቤቶችን አገልግሎቶች የተመለከቱ ጥያቄዎችን ጠይቀው መረጃ የሚያገኙበት የጥሪ ማዕከል ተጠቃሽ ነው።
6152 የጥሪ ማዕከል የሚሰጣቸው አገልግሎቶች👇
👉 የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ሁሉም ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ ለማወቅ
👉 በኢ-ፋይሊንግ የተከፈቱ መዝገቦች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ
👉 የተሰጠ ውሳኔን ለማወቅ
👉 የስማርት ችሎት አገልግሎቶችን ለማወቅ
👉 እንዲሁም ለፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል የሚያግዙ ጥቆማዎችና አስተያይቶች ለመስጠት ያገለግላሉ።
ስለሆነም፣ ከዛሬ ግንቦት 17 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ወደ 6152 የጥሪ ማዕከል በመደወል የፈለጉትን መረጃ ባሉበት ሆነው ማግኘት እንደሚችሉ እናስታውቃለን።



