ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎበኙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎበኙ

ባህርዳር ፣ ሚያዚያ 23/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ሎሜ በዶ፣ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሀረላ አብዱላሂ ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር ) እና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት ለተገልጋዩ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን የለውጥ ስራ፣ ምቹ የስራ ቦታ ፈጠራ እና በአጠቃላይ በክልሉ የዳኝነት እና የፍትሕ ሁሉ አቀፍ የለውጥ ስራዎች የተጀመሩ የመሰረተ ልማትና የአሰራር ማሻሻያ ለውጦችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የዳኝነት እና የፍትሕ አገልግሎት የለውጥና የማሻሻያ ስራዎችን በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በበላይነት የሚያስተባብሩ ሲሆን፣ ምክትል አፈ ጉባኤዋ እና ሌሎች ከፍተኛ ሀላፊዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለመመልከት በመጡበት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየተገበራቸው ያሉ አጠቃላይ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የለውጥና የማሻሻያ ስራዎችን ተመልክተዋል።

የባለጉዳዮችን ወጭ፣ እንግልት፣ ጊዜ እና ጉልበት በመቀነስ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ፣ ተገማች እና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመዘርጋት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸውን፣ የመሰረተ ልማት፣ ምቹ የስራ ከባቢ እና ሌሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎችን በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ገለጻ እና ማብራሪያ የተደረገላቸው ሀላፊዎቹ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባጭር ጊዜ ውስጥ ባከናወናቸው የማሻሻያ ስራዎች መደነቃቸውን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የለውጥ እና የማሻሻያ ስራዎች ለሌሎች የዳኝነት እና የፍትሕ ተቋማት አርአያ የሚሆኑ ናቸው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፣ የተጀመሩ ስራዎች የባለጉዳዮችን እንግልት የሚቀንሱ እንዲሁም የዳኞችን እና የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት የሚጨምሩ ናቸው ብለው፣ እስካሁን የተመዘገቡ መሰረታዊ የለውጥ ስራዎችን በላቀ ደረጃ አስቀጥሎ መሄድ እንደሚገባ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያይት ተናግረዋል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉብኝት ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

photo_1_2026-05-04_14-15-39
photo_3_2026-05-04_14-15-39
photo_4_2026-05-04_14-15-39
photo_5_2026-05-04_14-15-39
photo_6_2026-05-04_14-15-39
photo_7_2026-05-04_14-15-39
photo_8_2026-05-04_14-15-39
photo_10_2026-05-04_14-15-39
photo_9_2026-05-04_14-15-39

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *