ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በካቶሊክ የበጎ አድራጎት አገልግሎት የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዘመዴ ዘውዴ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አደረጉ

በካቶሊክ የበጎ አድራጎት አገልግሎት የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዘመዴ ዘውዴ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አደረጉ

ባህር ዳር ፣ ሚያዚያ 14 / 2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት)

በካቶሊክ የበጎ አድረጎት አገልግሎት የኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዘመዴ ዘውዴ ዛሬ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ተገኝተው በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

አቶ ዘመዴ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ጋር ተገናኝተውም በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ዉይይት አድርገዋል።

ፍ/ቤቱ የጀመረው የለውጥ ሥራ አካል የሆኑ የስማርት ኮርት፣ የኢ- ፋይሊንግ፣ ዲጅታል የአንድ ማዕከል የዳኝነት አገልግሎት እና ሌሎች የለውጥ ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ የጀመራቸው ዘርፈ ብዙ የለውጥ ሥራዎችን አስመልክቶ በአቶ አለምአንተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

አቶ ዘመዴ በበኩላቸው፣ ፍ/ቤቱ የጀመራቸው የለውጥ ሥራዎች አስደሳች መሆናቸውን እና ከጠቅላይ ፍ/ቤቱ ጋር አብሮ ለመስራት የሚቻልባቸውን ሁሉንም አማራጮች እንደሚያዩ ገልፀው፣ በጠቅላይ ፍ/ቤቱ የተመዘገበው የለውጥ ሥራ ውጤት በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ሞዴል ሊሆን የሚችል እና በሁሉም አካባቢዎች ሊሰፋ የሚገባው ነው ብለዋል።

photo_5_2026-04-22_15-36-36
photo_2_2026-04-22_15-36-36
photo_3_2026-04-22_15-36-36
photo_4_2026-04-22_15-36-36
photo_6_2026-04-22_15-36-36
photo_7_2026-04-22_15-36-36
photo_8_2026-04-22_15-36-36
photo_9_2026-04-22_15-36-36
photo_10_2026-04-22_15-36-36
photo_11_2026-04-22_15-36-36
photo_12_2026-04-22_15-36-36
photo_13_2026-04-22_15-36-36
photo_14_2026-04-22_15-36-36

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *