ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

“ከዓለምአቀፍ የሕግና ፍትህ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት በአገራችን እየተተገበሩ ያሉ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ የለዉጥ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር የጎላ ድርሻ አለዉ” ክቡር አቶ አለምአንተ አግደዉ – የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት

“ከዓለምአቀፍ የሕግና ፍትህ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት በአገራችን እየተተገበሩ ያሉ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ የለዉጥ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር የጎላ ድርሻ አለዉ” ክቡር አቶ አለምአንተ አግደዉ – የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት

ባህር ዳር ፣ ሚያዚያ 09/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደዉ የተመራ ልዑክ በተመረጡ የአውሮፓና የኤዥያ ሃገራት የዳኝነትና የፍትህ ተቋማት የሥራ ጉብኝት ሲያደርግ ቆይቷል።

የሥራ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ እንደ አገር እና በክልል ደረጃ የተጀመሩ የዳኝነት እና የፍትህ ዘርፍ የለዉጥ ሥራዎችን የበለጠ እያጠናከሩ ለመሄድ የሚያስችል ልምድ ለመዉሰድ መሆኑን የገለጹት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ በቀጣይም በተመረጡ መስኮች ላይ ከተቋማቱ ጋር በትብብር መሥራት የሚቻልበትን ምቹ መደላድል ለፍጠር መሆኑን ተናግረው ፣ በቆይታቸው ዉጤታማ ጉብኝነት እና ዉይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

የልዑክ ቡድኑ አባላት በሲንጋፖር ፤ በሆንግ ኮንግ ፣ በፈረንሳይ እና በኔዘርላድ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን የጉበኙ ሲሆን፣ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋርም ፍሬያማ ዉይይት አድርገዋል።

በሲንጋፖር ፤ የሲንጋፖር አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከል (Singapore International Arbitration Centre (SIAC) ፣ ማክስ ዌል ቻምበር (Max Well Chamber) እና የሲንጋፖር ጠቅላይ ፍ/ቤትን የጎበኙ ሲሆን ፣ በሆንግ ኮንግ ፤ የሆንግ ኮንግ አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከልን (Hong Kong International Arbitration Center (HKIAC)) ፣ አለምአቀፍ የሽምግልና ማዕከልን (International Organization for Mediation (IOMED)) ፣ የሆንግ ኮንግ አለምአቀፍ የሕግ ማሰልጠኛ ተቋም (Hong Kong International Legal Talent Training Office) እና የሆንግ ኮንግ ዲፓርትመንት ኦፍ ጀስቲስን እንዲሁም ፤ ከአዉሮፖ አገራት የፈረንሳይ ሁለት አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከላትን (International Chamber of Commerce እና Paris Arbitration Center) ፤ በኔዘርላድስ ዓለምአቀፍ ቋሚ የግልግል ፍ/ቤትን (Permanent Court of Arbitration) እና በዘ ሄግ አለምአቀፍ የሕግ ትምህርት ተቋም (The Hague International Law Academy) ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ክቡር አቶ አለምአንተ አግደዉ፣ ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ከሲንጋፖር አለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስ ግሎሪያ ለም ፣ ከአለምአቀፍ የሽምግልና ማዕከል ሴክሬታሪ ጀነራል ፕሮፌሰር ተርሳ ቺንግ ፣ ከሆንግ ኮንግ አለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆዋኒ ላኡ፣ ከሆንግ ኮንግ አለምአቀፍ የሕግ ማሰልጠኛ ተቋም የአለምአቀፍ ህግ ጉዳዮች ኃላፊ ጄምስ ዲንግ (ዶ/ር) ፣ በፈረንሳይ ከአለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከል ፕሬዝደንት ሚስ ክላውዲያ ሳሎሞን ፣ ከፓሪስ የግልግ ዳኝነት ማዕከል ፕሬዘዳንት ሚስተር ሃፌዝ ቨርጅ ፣ ከዓለምአቀፍ ቋሚ የግልግል ፍ/ቤት ምክትል ሴክሬታሪያት ጀነራል ሚስተር ጋርት ስኮፊልድ እና ከ ዘ ሄግ አለምአቀፍ የሕግ ትምህርት ተቋም ምክትል ሴክሬታሪያት ጄነራል ሚስ አና ቫሲልቫ እንዲሁም በግልግል ዳኝነት ላይ ከሚሰሩ የተወሰኑ የጥብቅና ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ፣ በዉይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመሩ እና የተሰሩ ሰፋፊ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ እና ሁለንተናዊ የተቋም ግንባታ የለዉጥ ሥራዎች፣ ተደራሽ እና ዉጤታማ የዳኝነት ስርዓት ለመገንባት እና ፍ/ቤቶችን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በተለይም አማራጭ ያለመግባባት መፍቻ ሥርዓቶችን ለማጠናከር እንደ አገር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ፣ በፍ/ቤቶች የተመዘገቡ የለዉጥ ሥራ ዉጤቶችን እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች እና የትብብር መስኮችን አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ አቅርበዋል፡፡

በተለይም አመራጭ ያለመግባባት መፍቻ ስርዓቶችን ለማጠናከር በተያዘዉ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ ዕቅድ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት እና የሌሎች አለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ መሆኗ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለምአቀፍ ትስስር የፈጠረላት መሆኑን ፣ አገሪቱ የትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት እና ሰፋፊ የኢኮኖሚ፣የሕግና የተቋም ግንባታ ማሻሻያ ዉስጥ እያለፈች መሆኗ ኢትዮጵያን የግልግል ዳኝነት ማዕከል ለማድረግ ለተጀመረዉ ሥራ አስቻይ ሁኔታዎች በመሆናቸዉ አለምአቀፍ የሕግና የፍትህ ተቋማት እንዲሁም አገራቱ በትብብር መስራታቸዉ ለሁሉም ጠቀሜታዉ የጎላ እንደሚሆን ገልፀዉ ፣ በሁሉም አካላት ለተደረገላቸዉ አቀባበል እና መስተንግዶ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአለምአቀፍ ተቋማቱ አመራሮች በበኩላቸዉ እንደ አገር በኢትዮጵያ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ እንዲሁም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተጀመሩ የለዉጥ ሥራዎችን ዉጤታማነት አድንቀዉ ፣ በቀጣይ በባለሙያ አቅም ግንባታ፣በቴክኒክ ድጋፍ እና ልምዶችን በማጋራት ረገድ አብሮ ለመስራት ያላቸዉን ፍላጎት ለክቡር ፕሬዘዳንቱ አረጋግጠዉላቸዋል፡፡

photo_17_2026-04-20_07-48-32
photo_1_2026-04-20_07-48-32
photo_2_2026-04-20_07-48-32
photo_2_2026-04-20_07-48-32
photo_3_2026-04-20_07-48-32
photo_13_2026-04-20_07-48-32
photo_5_2026-04-20_07-48-32
photo_7_2026-04-20_07-48-32
photo_8_2026-04-20_07-48-32
photo_6_2026-04-20_07-48-32
photo_9_2026-04-20_07-48-32
photo_10_2026-04-20_07-48-32
photo_11_2026-04-20_07-48-32
photo_12_2026-04-20_07-48-32
photo_15_2026-04-20_07-48-32
photo_16_2026-04-20_07-48-32
photo_18_2026-04-20_07-48-32

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *