ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በኢትዮጵያ የቱርክዩ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር በርክ ባራን ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ጋር በጋራ በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ ተወያዩ

በኢትዮጵያ የቱርክዩ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አምባሳደር በርክ ባራን ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ጋር በጋራ በሚሰሩበት ጉዳይ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29/2018 (አብክመ ጠ/ፍ/ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት በመሰረታዊነት ለማሻሻል በስርነቀል የለውጥ ሂደት ውስጥ እያለፈ ይገኛል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን ፍርድ ቤት እንዲሁም የፍትሕ ስርዓቱን ጠንካራ እና የህብረተሰቡን አመኔታ ያረጋገጠ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህንንም ለማጠናከር ይረዳ ዘንድ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር አገልግሎቶችን በማዳበር ላይ ይገኛል፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ከቱርክዬ አምባሳደር በርክ ባነር ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ተምሳሌት የሆነ ፍርድ ቤትን የመገንባት ርዕዩን በመግለፅ ለዚህም የክልሉን ፍርድ ቤቶች ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከአካላዊ ተደራሽነት ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ ተደራሽነት በማረጋገጥ የዘመናዊ ዳኝነት መስጫ ማእከል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችን፣ አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓቶችን ማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት እና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለውን ሚና በተለይ ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን እውቅና አሰጣጥ እና አደረጃጀት እንዲሁም በእነዚህ ተቋማት ላይ የሚሰራ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰቶት እየተተገበረ ስለመሆኑ፣ በሰው ሀይል አቅም ግንባታ ዘላቂነት እንዲኖረው ትኩረት መሰጠቱ እንዲሁም የተጀመረውን ሁሉአቀፍ የለውጥ እና የማሻሻያ ስራ አስመልክቶ ውጤታማ የሆነ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ክቡር አምባሳደሩም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየሰራ ያለውን የለውጥ ተግባራት ያስገረማቸው መሆኑን በመግለፅ፣ እስካሁን የታየው ሂደት እና የተያዙት እቅዶች በግልጽ አተገባበር ስርዓት የተቀመጠላቸው መሆኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የያዘውን ርዕይ ለማሳካት ጉዞ ላይ መሆኑን መረዳታቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጀመራቸው ስራዎች ውስጥ በማገዝ እና በመተባበር ውጤታማ መሆን እንደሚቻልም አስቀምጠዋል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፣ አምባሳደሩ ጊዜ ሰጥተው የፍርድ ቤቱን እቅድ በመረዳት እንዲሁም በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አመስግነው፤ በክልሉ ተምሳሌት የሆኑ ፍርድ ቤቶችን ለመገንባት ርዕይ ሰንቆ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ አካል በመሆን በክልሉ ፍትህ ስርዓት ውስጥ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Screenshot
Screenshot

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *