ብራሰልስ ፣ መጋቢት 21/2018 (የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት)
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት አለምአንተ አግደው እና የልዑክ ቡድናቸው ከሥራ ጉብኝታቸው ጎን ለጎን በብራስልስ ቤልጅየም የኢትዮጵያ ኤምባሲን የጉበኙ እና ዉይይት ያደረጉ ሲሆን ፣ ፕሬዘዳንቱ የኤምባሲው ዲፕሎማቶች በአገር ደረጃ የተያዙ የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ የለውጥ ሥራዎች ከአለምአቀፍ የሕግ ተቋማት ተገቢውን ድጋፍ እና ትብብር በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት ይገባቸዋል ብለዋል።
ኤምባሲውን ያስጎበኙት እና በውይይቱ የተገኙት በቤልጅየም የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ በበኩላቸው፣ በልዑኩ ጉብኝት ወቅት ከአለም አቀፍ የሕግ ተቋማት ጋር ዉይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ድጋፍ በሚገኝበት ሁኔታ ላይ ኤምባሲው ትኩረት ሰጦ እንደሚሰራ እና እንደ አገር የተያዘው የዳኝነትና የፍትህ ዘርፍ የሪፎርም ሥራ ላይ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
