በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰብሳቢነት የሚመራውና ሁሉም የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች አባል የሆኑበት አገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬድዋ ከተማ የተካሄደ ሲሆን እስከ ጥቅምት 13 በደሬድዋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች :በሃረሪ እና ሱማሌ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶች የተሰሩ የፍ/ቤት ሕንፃ እድሳት እና የዲጅታላይዜሽን ሥራዎችን ጉብኝትመእ አካሂዷል።
በመድረኩ የተሳተፉት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው እንደገለፁት በመድረኩ የቀረቡ ሪፖርቶችና ውይይቶች ሲታዩ በሁሉም ፍ/ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ውጤታማ ለማደረግ የተሰሩ ሥራዎች እጅግ አበረታች መሆናቸውን፣
በፌደራልም ሆነ በክልሎች ደረጃ ፍ/ቤቶችን በሰው ሃይል ፣ በበጀት እና በቴክኖሎጅ ለማጠናከር የተሰሩ ሥራዎች ለዚህም የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት እያሳዩ ያሉት ቁርጠኝት ከፍተኛ እውቅና ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል።
ሁሉንም ፍ/ቤቶች ወደ ተቀራራቢ የዳኝነት የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ለማምጣት በፍ/ቤቶች መካከል ያለው የእርስ በእርስ መደጋገፍ እና ትብብር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሯል ፤ በተለይም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዲጅታላይዜሼን ሥራዎች በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፋ ላደረገው ድጋፍ ሊመሰገን ይገበዋል ብለዋል ።
ክቡር ፕሬዘዳንቱ አያይዘውም ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የጋራ መድረኩ እየተጠናከረ እንዲሄድና በየአካባቢው ካሉ መልካም ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶች ልምድ በመውሰድ ለህብረተሰባችን የተሻለ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት በፍ/ቤት ላይ ያለውን አመኔታ ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
