ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል  ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሕ ሙዚየምን በይፋ መርቀው ከፈቱ

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል  ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሕ ሙዚየምን በይፋ መርቀው ከፈቱ

ባሕርዳር፣ ነሐሴ 28/2018 ( የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በሁሉ አቀፍ የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚገኘው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመን ተሻጋሪ የዳኝነትና የፍትሕ ተቋማትን በመገንባት ላይ ይገኛል።

ለዳኞች፣ ለሰራተኞችና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ምቾትን የሚሰጡ የስራ ከባቢዎችን፣ ሙያዊ አቅምና ሥነ-ምግባር የተላበሱ ዳኞችን እና ሰራተኞችን ለማፍራት በርካታ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እና የትምሕርት እድሎችን እያመቻቸ ያለው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ ከዘመናዊ የዳኝነት ተቋማት እና የሰው ሀይል ግንባታው በተጨማሪ በዳኝነት እና ፍትሕ ዘርፉ የተመዘገቡ ታሪካዊ የጊዜ እና የሁነት ክስተቶችን መዝግቦ መያዝ የሚያስችለውን የፍትሕ ሙዚየም ገንብቷል።

ግንባታውን ለማከናወን፣ ለሙዚየሙ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ እና ለማደራጀት አንድ ዓመት የወሰደ ሲሆን፣ ሙዚየሙን የማደራጀት ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የፍትሕ አካላት ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት ሙዚየሙን በይፋ መርቀው የከፈቱት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ናቸው።

በሙዚየሙ የዳኝነት እና የፍትሕ ዘርፍ ታሪካችንን በአንድ ማእከል አይተናል ያሉት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ በፍርድ ከሄደች በቅሎየ ያለፍርድ የሄደች ጭብጦየ በሚለው አባባሉ ለሚታወቀው እና ለሕግ እና ፍትሕ ትልቅ አመለካከት ላለው ማሕበረሰባችን ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ነው ብለዋል።

ሙዚየሙ ለወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሂደት ትልቅ ማስተማሪያ የሚሆን ነው ያሉት ክቡር ርዕሰ መስተዳደሩ፣ ለጥናት እና ምርምር አጋዥ ማዕከል ይሆናል ብለዋል።

የሙዚየሙ በዚህ መልኩ መደራጀት የሕብረተሰባችን የማንነት መገለጫ የሚሆን ነው ያሉት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ መዚየሙን ላደራጁት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *