ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የፌደራል እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች የጣና ሀይቅ ገዳማትን እና ባሕር ዳር ከተማን ጎበኙ

የፌደራል እና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች የጣና ሀይቅ ገዳማትን እና ባሕር ዳር ከተማን ጎበኙ

ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 02/2019 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የሀገር አቀፍ የሕግ ተርጎሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።

የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስን ጨምሮ፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች እና የአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች የጣና ሀይቅ ደሴቶችን እና በባሕር ዳር ከተማ የተሰሩ መሠረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል።

በብዙ ደሴቶች እና ገዳማት የተከበበውን የጣና ሀይቅ የጎበኙት ፕሬዘዳንቶቹ፣ የክብራን ገብርኤል ገዳም በመገኘት ቀደምት የሆነውን ቤተክርስቲያን እና በስፍራው የሚገኙ ቅርሶችን ጎብኝተዋል።

ፕሬዝደንቶቹ በባሕር ዳር ቆይታቸው፣ በከተማዋ የሚገኙ መሠረተ ልማቶችን የጎበኙ ሲሆን፣ የባሕር ዳር አለም አቀፍ ስቴዲየምን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከባህርዳር አለምአቀፍ ስታዲዮም በተጨማሪ፣ የአባይ ድልድይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋን መሰረተ ልማቶች ተመልክተዋል።

ባዩት ነገር የተደነቁ መሆናቸውን የገለጹት ፕሬዘዳንቶቹ፣ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *