ባሕር ዳር፣ ጥቅምት 01/2019(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የሀገር አቀፍ የሕግ ተርጎሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ነው።
የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስን ጨምሮ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች እና የአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንቶች፣ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የክልሉን ፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ በመሰረታዊነት ለማሻሻይ እየተገበራቸው ያሉ አሰራሮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዳኝነት አገልግሎቱን በማዘመን ተደራሽነትን ለማስፈት የሰራቸው የስማርት ችሎት፣ የኢ -ፋይሊንግ፣ የአንድ ማእከል ዲጂታል አገልግሎት እና የጥሪ ማእከል ጎብኝተዋል።
ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር የተሰሩ ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች በጉብኝቱ የተካተቱ ሲሆን፣ የዳኝነት እና የፍትሕ አካላትን ታሪክ ሰንዶ ለማቆየት፣ ለሕግ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የመረጃ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተገነባውን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፍትሕ ሙዚየም ተመልክተዋል።
ፕሬዝደንቶቹ በጉብኝታቸው፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎትን ተደራሽነት ለማስፋት የሰራቸው ሥራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ልዩ ጉባኤ ለመታደም ባህርዳር የተገኙት ፕሬዝደንቶቹ፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ የጣና ሀይቅን እና ባሕር ዳር ከተማን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።












