ASC Logo

አማራ ክልል 

ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትን የጎበኙ የክልል ቢሮ ሃላፊዎች የፍርድ ቤቱን የለውጥ ሥራዎች አድንቀው፣ ተሞክሮው ወደ ሌሎች ተቋማትም ሊሰፋ የሚገባው መሆኑን ገለጹ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትን የጎበኙ የክልል ቢሮ ሃላፊዎች የፍርድ ቤቱን የለውጥ ሥራዎች አድንቀው፣ ተሞክሮው ወደ ሌሎች ተቋማትም ሊሰፋ የሚገባው መሆኑን ገለጹ

ባሕር ዳር ፣ ነሃሴ 10 /2018 ( የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት)

የአማራ ክልል የእንስሳት እና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ክቡር ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) እና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ደረጀ ማንደፍሮ  የጠቅላይ ፍ/ቤቱን የለውጥ ሥራዎች የጎበኙ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ወቅት የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዘዳንት የተከበሩ አቶ ዓለምአንተ አግደው ስለተሰሩ የለውጥ ሥራዎች ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ቢሮ ሃላፊዎች በጉብኝታቸውም በፍ/ቤቱ ከተሰሩ የለውጥ ሥራዎች መካከል በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፣ በሁሉም ከፍተኛ ፍ/ቤቶች እና በተመረጡ ወረዳዎች የተሰሩ ሰፋፊ የዲጅታይዜሽን ሥራዎች፣ በጠቅላይ ፍ/ቤት እና በሁሉም ከፍተኛ ፍ/ቤቶች እንዲሁም በተመረጡ ወረዳዎች ከአንድ ማዕከል ቁጥጥር የሚደርግባቸው የደህንነት ካሜራ ሥርዓቶች ፣ የተሻሻሉ ነባር እና አዲስ የህንፃ ግንባታዎች፣ የርቀት ክርክር እና የኢ-ፋይሊንግ አሰራሮች ፣ የመረጃ አቅርቦት አማራጮች ( ነፃ የጥሪ ማዕክል፣ የሞባይል መተግበሪያ፣ ዌብ ሳይት፣ ዲስፕሌይ ስክሪኖች እና መረጃ መስጫ ቲወክሶች፣) ፣ ስቹየሽን ሩም ፣ የፍትህ ሙዚየም ፣ የህፃናት ማቆያ፣ የሚያጠቡ ባለጉዳይ እናቶች እና የአቅመ ደካሞች ማረፊያ ፣ ለአካል ጉዳተኞች የተመቻቹ አሰራሮች ( በአጠቃላይ ሰው ተኮር የለውጥ ሥራዎችን) ፣ ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የመኪና እና ብስክሌት ማቆሚያ ቦታዎች፣ የሾፌሮች ማረፊያ ፣ ዘመናዊ የሠራተኞች ካፌን፣ ምቹ የሥራ ቦታዎችና የግሪነሪ ሥራዎች እና ሌሎችን ጎብኝተዋል ።

ቢሮ ሃላፊዎቹ ከጉብኝቱ በሁዋላ በሰጡት አስተያየት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በተለይም ፕሬዘዳንቱ ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የዜጎችና የተገልጋዮችን ህይወት በሚያቀል መልኩ መሬት የነኩ እና ለትውልድ የሚተላለፉ ተጨባጭ የለውጥ ሥራዎች ሃሳብ በማመንጨት እና በአጭር ጊዜ በልዕቀት በመተግበር የተገልጋዮችን እንግልት እና ወጭ በሚቀንስ እንዲሁም ፍትሕን በከፍተኛ ደረጃ ተደራሽ በማድረግ ለሰሩት ሥራ ከፍተኛ አድንቆት እና ክብር ያለቸው መሆኑን ገልፀዋል ።

የተሰራው የለውጥ ሥራ በሁሉም የክልሉ ተቋማት ከዚያም አልፎ ለሌሎች በተሞክሮነት የሚወሰድ በመሆኑ ሁሉም ሊያየው ይገባል ብለዋል።

ስለለውጥ ሥራው በተለያየ ጊዜ በሚዲያ የተገለፀ ቢሆንም ይሄ በቂ እንዳልሆነና በአካል ሲታይ በሚዲያ ከሚሰማው በላይ ግዙፍ የለውጥ ሥራ የተሳካበት ነው ሲሉ አክለዋል።

ክቡር አቶ አለምአንተ በበኩላቸው፣ ቢሮ ሃላፊዎቹ በመገብኘታቸው እና ለሰጡት ገንቢ አስተያየት አመሰግነው፣ ፍ/ቤቱ የተጀመረውን የለውጥ ሥራ ዘላቂ እንዲሆን አበክሮ እንደሚሰራና ሌሎች አዳዲስ የለውጥ ፕሮግራሞችንም በቀጣይ እንደሚያስተዋውቅ እና እንደሚያስጀምር ገለፀው፣ እንደ ክልልም ሆነ በአገር ደረጃ ተቋም ግንባታ ላይ አበክሮ በመስራት አገርን በሁለንተናዊ መልኩ ማሳደግ ላይ ሁሉም ተባብሮ መስራት ያለበት መሆኑን እና ፍ/ቤቱ በተሰጠው ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮ መሰረት የድርሻውን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *